Get Mystery Box with random crypto!

Ashara Media - አሻራ ሚዲያ

የሰርጥ አድራሻ: @ashara_media
ምድቦች: ክሪፕቶ ምንዛሬዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 48.75K
የሰርጥ መግለጫ

ስልክ፥ 251984190114 / 251993111700

Ratings & Reviews

4.50

0 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-06-25 19:26:35 የአማራ ፋኖ በጎጃም ድሎች

የአማራ ፋኖ በጎጃም ሰራዊት በአዴት እና መርዓዊ ግንባር የአገዛዙን ሰራዊት ከጥቅም ውጭ አደረገ
በክልሉ ርዕሰ ከተማ ባህርዳር በቅርብ ርቀት ላይ ባሉ አካባቢዎች ውጊያዎች ቀጥለዋል፡፡
በበርካታ ግንባሮች በቀጠሉ ውጊያዎች የአማራ ፋኖ በጎጃም ሰራዊት አንደኛ ክፍለ ጦር በሰራው ልዩ ኦፕሬሽን አዴት ከተማን ተቆጣጥሮ የነበረ ሲሆን በርካታ የአገዛዙ ወታደሮችን ከጥቅም ውጭ አድርጓል፡፡
የአንደኛ ክፍለ ጦር የጀነራል አሳምነው ጽጌ ብርጌድ በሰራው ከባድ ኦፕሬሽን ከፍተኛ ድል መመዝገቡን የአማራ ፋኖ በጎጃም ቃል አቀባይ ፋኖ ማርሸት ጽሐው ተነግሯል፡፡
ፋኖ ማርሸት ለጊዮን ሚዲያ በሰጠው ቃል በአዴት ከተማው ኦፕረሽን የመከላከያ መለዮለባሽ የብርሃኑ ጁላ ወታደሮች ሲደመሰሱ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የሚሊሻ አባላት እጅ ሰጥተዋል  ብሏል፡፡
ድሽቃ የጫነ ፓትሮል ሙሉ በሙሉ ወድሟል ያለው ቃል አቀባዩ የፋኖ ሰራዊት ትናንት ከጠዋት12 ሰዓት እስከ ቀኑ ሰባት ሰዓት ድረስ አዴት ከተማን በመቆጣጠር የሚፈልገውን ወታደራዊ ተልዕኮ ከጨረሰ በኋላ በከፍተኛ የሃላፊነት ስሜት ከተማ ውስጥ ውጊያ እንዳይደረግ በሚል ለህዝብ ደህንነት በማሰብ የአገዛዙ ጦር በሌለበት ቀድሞው መመለሱም አስረድቷል፡፡
በትናንቱ ኦፕሬሽን ስለተገኙ ምርኮዎች መረጃ በመስጠትም የአማራ ፋኖ በጎጃም ሰራዊት በባህርዳር ቅርብ ርቀት ባሉ ከተሞች የማጥቃት እርምጃዎችን በመውሰድ የአገዛዙ ጦር አከርካሪ በመስበር ላይ እንደሚገኝ ፋኖ ማርሸት አክሏል፡፡
ቃል አቀባዩ በተያያዥ ሌላ  ጉዳይ ኗሪነታቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ የአማራ ተወላጅ ባለሀብቶች ዘረፋ እየተፈጸመበቸው እንደሆነ በማስመሰል በፋኖ ላይ ተቃውሞ እንዲያሰሙ በአገዛዙ እየደረሰባቸው ያለው ጫና ከፍተኛ መሆኑን አንስቷል፡፡
በዚህም ባለሀብቶች ለሁለት መከፈላቸውንና ጉዳዩ መወሳሰቡን ፋኖ ማርሸት ገልጧል፡፡
5.6K viewsአባ ስበር, 16:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-25 16:27:56
ዶር ገዱ አንዳርጋቸው እና ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት በትናንትናው እለት ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ምንስትር ሀላፊዎች ጋር መወያየታቸው ታውቋል። በውይይቱም የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ መሠረታዊ ለውጥን የሚጠይቅ መሆኑን አንስተው የቀጠናው ሁኔታ ከመወሳሰቡ በፊት በኢትዮጵያ ሁሉን አካታች የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም ለሚደረገው ጥረት የአመሪካ መንግስት ከኢትዮጵያዊያን ጎን እንዲቆም ጠይቀዋል።በአማራ እና አጠቃላይ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታና የመውጫ መንገድ የሚያስረዳ ሰነድ ለአሜሪካ መንግስት ማቅረባቸው ታውቋል።
8.7K viewsኢትኤል, 13:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-25 15:39:21
የጨነቀለት
8.7K viewsኢትኤል, 12:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-25 14:32:34 አሳዛኝ መረጃ

በርካታ አማራዎች በተለያዩ አካባቢዎች የፋኖን በትር መቋቋም በተሳነው በአብይ አህመድ አራዊት ሰራዊት በግፍ እየተረሸኑ ነው። በትናንትናው ዕለት በርካታ ወጣቶች ከሰባታሚት ማረሚያ ቤት አወጥተው አዴት መድሃኒዓለም  አካባቢ አደባባዩ ጋር ተረሽነዋል። ፋኖ ጥቃት ሲያደርስባቸው ቀጥታ የፈሪ ዱላቸውን ንፁሀን ላይ ማድረግ የተለመደ ተግባራቸው ሁኗል።
9.3K viewsኢትኤል, 11:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-25 10:45:02
በአብይ አህመድ ቤት ከሱ በላይ አራዳ የለም። ጠቡን በአማራ ብልፅግና በፋኖ መካከል ይመስል አንዴ አዲስ አበባ ሌላ ጊዜ ባህር ዳር ሆዳቸውን ወክለው ለአብይ አህመድ ከሚላላኩ ኩሊዎች ጋር ህዝብ አወያየን እያሉ ነው።

የፋኖ ጠብ ከራሱ አብይ አህመድና ከሚመራው ብልፅግና ጋር ነው። ክልሉ እንዲላላኩ ካስቀመጣቸው ደንገጡሮች ጋር የሚደረግ ውይይት ጉንጭ ከማልፋት ውጭ ሌላ አንዳች ለውጥ አያመጣም።
10.5K viewsኢትኤል, 07:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-24 08:10:58 አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በሚል የዳቦ ስም አማራን ለመጨፍጨፍና ለማውደም በክልሉ የገባው የብልጽግና መራሹ የብርሀኑ ጦር ትናት በእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ;በሰኞ ገበያ እና አካባቢው በሚገኙ ቀበሌዎች ደብረ መዳኒት ወሪያ መስቀል በረሀማ የገጠር ቀበሌዎችን ከጠዋቱ 12ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ 6:00 ድረስመንደሮችን ሲደበድብ ውሏል በዚህም በአካባቢው የነበሩ ህፃናትን ጨምሮ በርካቶች በግፍ ተጨፍጭፈዋል ከሞት የተረፉት ቂያቸውን ለቀው ተሰደዋል ።በእለተ ሰንበት ይደረግ የነበረው የቅዳሴ ሀይማኖታዊ ስርዓት ሲስተጓጎል አብያተ ቤተክርስቲያናት ተዘግተዋል።የአማራ ፋኖ በጎጃም የሳሙኤል አወቀ ክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት ፋኖ ባየ ደስታ ashara media
13.3K viewsአባ ስበር, edited  05:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-24 07:20:58 የአማራ ፋኖ በጎጃም የሳሙኤል አወቀ ክ/ጦር በአረንዛው ጎንቻ ብርጌድ ጦር አዛዥ አውለው ደምስና የብርጌዱ ዘመቻ 50አለቃ ውዱ ተሾመ የተመራው ልዩ ኦፕሬሽን በተቀናጀ መልኩ ጠላትን አንገት ያስደፋ ገድል ፈፅመዋል።
በክፍለ ጦሩ የሚንቀሳቀሱት የአረንዛው ጎንቻ ብርጌድ ሁለቱ ሻለቃዎች ማለትም ታምረኛው ባህረ ጊዩርጊስ ሻለቃና ነበልባሉ እነጎዴ ሻለቃ ከአባይ ሸለቆ ብርጌድ የተመረጠ መች ኃይል ጋር በጥምረት በተወሰደ ኦፕሬሽን በግንደወይን ከተማ ጅምር የሆስፒታል ግንባታ ውስጥ የመሸገውን ሀይል ከረፋዱ 4:00 በተቀመጠበት ከበባ በማድረግ የጠላት ኃይል ተደምስሷል ። የፋሽሽቱ ሰራዊት በተወሰደበት ኦፕሬሽን አንድ የ ሬጅመንት ና ሻንበል መሪ ሲደመሰሱ በራካታ ቁጥር ያለው ሰራዊቱ በከተማው ዙሪያ ባለው ጥቅጥቅ ጫካ በጅምላ መቅበሩም ታውቋል። ከድንጋጤው መውጣት ያልቻለው የ71ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ ኮ/አዱኛውን እና ታማኝ ካድሪዎቹ ቤት ተዘግቶባቸው ልዩ ጥበቃ የተደረገላቸው ሲሆን ግንደወይን ከተማም የእንቅስቃሴ ገደብ ተጥሎባት ማንኛውም ተሽከርካሪ ሱቆችንና ሆቴሎች ጨምሮ ሙሉ ለሙሉ አገልግሎት እንዳይሰጡ ተደርጓል።ይሁን እንጅ
ጫካም ይሁን ተራራ በፀራራ ፀሀይም ይሁን በድቅድቅ ጨለማ ጠላትን እያናጠሉ የመምታት ኦፕሬሽን ተጠናክሮ ስለሚቀጥል ጠላት የሚደርስበትን ምት መቋቋም ሲያቅተው ንፁሃንን አየገደለ በቀሉን ስለሚወጣ ህዝባችን በጦርነቱ ጉዳት እንዳይደርስበት ጥንቃቄ እንዲያደርግ እናሳውቃለን።
የአማራ ፋኖ በጎጃም ሳሙኤል አወቀ ክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት
ፋኖ ባየ ደስታ
Ashara media
13.1K viewsአባ ስበር, edited  04:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-24 05:12:02 ጣሊያንን ያሸነፍን አማሮች የኦሮሞ ልዩ ኃይል መጣንልህ የሚለን የት ሄደን ነው?????


አጣዬ እዚህ ቦታ ነበረች!


ዳዊት በጋሻው ጥላሁን
ቃሊቲ እስር ቤት



የአጣዬ ከተማ በብልጽግና ትዕዛዝ በወደመችበት ጊዜ ከሙያና ትግል አጋሮቼ መዓዛ መሐመድ ፣ ጎበዜ ሲሳይ ፣ ሙሉጌታ አንበርብር ፣ በላይ ማናዬና ምስጋናው ከፈለኝ ጋር ሆነን ወደ ከተማዋ ስንገባ  አጣዬን አጣናት። የሙያና የትግል ብሎም የእስር ቤት ጓዴ ጎበዜ ሲሳይ ከአጣዬ ጉብኝታችን በኋላ "አጣዬ እዚህ ቦታ ነበረች" የሚል አንጀት የሚበላ ዘገባ አሰማን። ሁላችንም እውነትም አጣዬ እዚህ ነበረች ብለን ከንፈር መጠጥን።
ኦነግም ብልጽግናም ያቃጠሏት አጣዬን ካየን በኋላ ሁላችንም የድምጽና የምስል ዘገባ ይዘን ተመለስን። ከአጣዬ ወደ አዲስ አበባ  ስንመለስ በመተከልና በወለጋ፣ በአርሲ፣ በሀረርጌ፣ በባሌ፣ በቡኖ በደሌ ተጨፍጭፈን፤ በአዲስአበባም አልቀረልንም። ከተሞቻችንን ማዳንና ማትረፍ፤ ህዝባችንንም መጠበቅ ያልቻልነው ለምን ይሆን ብለን በሰፊው ተወያዬን።
የውይይታችን መቋጫ ግን አከራካሪ አልነበረም።
እኛ አማራዎች ደጃዝማች ፀሐዩ እንቁስላሴ ከ 50 ዓመት በፊት የመከሩንን አለመተግበራችን ነው ብለን ተስማማን
ደጃዝማች ፀሐዩ በወቅቱ የነበረው ሁኔታ ተረድተው እንዲህ ብለው ነበር።

ከእንግዲህ ወዲህ ማንም ቢመጣ ተነሳሁ የሚለው አማራው ሕዝብ ላይ እንጅ ለይቶ የሸዋ፣ የጎንደር፣ የጎጃምና የወሎ አይልም። እኛም ወደድንም ጠላንም፤ የአማራው አንገት አንድ መሆኑን መወቅ አለብን ስለዚህ አማራው መተባበር አለበት ብለው ነበር። ግማሽ ክፍለዘመን ያለፈው ይህ ምክር አሁን የህልውና ትግል ውስጥ ላለነው ሁሉ የሚያገለግል ስንቅ ነው።
ሁሉም ጸረ አማራ ኃይሎች የሚያጠቁን በአማራ ማንነታችን እንጅ በተወለድንበት መንደር አሊያም በያዝነው ሃይማኖት አለመሆኑን ማስታወስ አለብን።
የመጥፋት አደጋ የተጋረጠበት ሕዝብ ተሰባስቦ እንጅ ተበታትኖ ሊድን ከቶ አይቻለውም።
አሁን ብልጽግና በድሮንና በጀት እየደበደበ ያለው ሁሉንም የአማራ ግዛቶች ከመሆኑም በላይ ወደፊት ያቀደውም ከዚህ የከፋ ስለመሆኑ እየነገረን ነው። ዐቢይ አህመድ ከ 10 ቢሊዮን ዶላር በላይ ሀብት አለኝ እዋጋለሁ ብሎ የዛተውን ማስታወስ በቂ ይሆናል።

አንድ አክቲቪስትና የፖለቲካ ሰው ተከበብኩ ሲል፤ አርቲስት ሲሞት...የአማራ እናት ነፍሰ ጡር ሆዷ እየተቀደደ የምትገደለው አማራ ስለሆነች ብቻ ነው። ሌላ ምክንያት የለውም። ከዚህ በላይ ግፍና ስቃይ ከየት ሊመጣ ይችላል ? የምንታገለው ለህልውና ነው ስንል የምራችንን ነው። ከዚህ ለመውጣት ደግሞ መተባበርና አንድ መሆን ግደታችን ነው። በተናጠል በሚደረገው ሩጫ፤ በግል በሚደረግ ጥረት ስር የሰደዱ ጠላቶቻችንን ማሸነፍ አይቻለንም። የግድ አንድ መሆንን ማስቀደም አለብን። እንደ ግለሰብ የምንከበረው እንደሕዝብ ስንከበርና አንድነታችን የጸና  ሲሆን ነው። ሕዝባችን በአንድነት ሲከበር ያኔ ሁሉም በግሉ ቀና ብሎ ይሄዳል። በዚህ ወቅት እርስ በእርስ መገፋፋትና መናናቅ ብሎም መሰዳደብ እኛን ከማስገመቱም በላይ እውን የአባቶቻችን ልጆች ነን ያስብላል።
ደራሲና የውጭ ግንኙነት ባለሙያ ሀዲስ አለማየሁ በጣሊያን ጦርነት ወቅት ሰዎች ጣሊያንን መዋጋት ትተው እርስ በእርስ ሲጣሉና ሲቆራቆሱ ቢመለከቱ" ውሾች ሌት ጅብ ሲመጣባቸው እሱን ለመቃወም ይተባበራሉ ፤ ታዲያ ከውሾች የሚሻሉት ሰዎች የጋራ ጠላታቸው ሁሉንም እያጠቃቸው ሲመጣ እያዩ ተባብረው ያንን የጋራ ጠላታቸውን በመቃወም ፋንታ እንደት እርስ በእርሳቸው ለመፋጀት ይነሳሉ? ሲሉ ጠይቀው ነበር። እኔም ይህንን ጥያቄ ደግሜ አነሳለሁ።

እዚህም እዚያም አለመግባባቶችና ጭቅጭቆች እንዳሉ እሰማለሁ። አለመግባባቶች መኖራቸው በራሱ ችግር ላይኖረው ይችላል ነገር ግን በህዝባችን ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሞበትና ደጃፉ ላይ ድሮንና ጀት እየተተኮሰበት እያየንና እየሰማን እርስ በእርስ መዘላለፍና እልህ መጋባት ተገቢ ካለመሆኑም በላይ የህሊናም የታሪክም ተጠያቂ ያደርገናል።
አሁን በግልጽ ቋንቋ በጋራና በአንድነት መታገልና የሕዝብ ጫንቃ ላይ የተለጠፈውን የፋሽስት ቀንበር ማንሳት ከዚህ ትውልድ ይጠበቃል። የአንድነትና የህብረትን ጠቀሜታ ለእናንተ ማስረዳት ለእናቷ ምጥ እንዳስተማረችው ልጅ መሆን ነው፤ ነገር ግን ለማስታወስ ያህል ይህንን ጹሑፍ ከእስር ቤት ልኬያለሁ።
የአማራ ህዝብ አገርንና መንግስታትን ያሻገረ የሚታይና የሚጨበጥ ስልጣኔ ያለው ከፈጣሪው ትዕዛዝ የማይወጣ ጨዋ ስብዕና ያለው ሆኖ ሳለ በጅምላ እንደ ወንጀለኛ መታየት ከጀመረ ግማሽ ክ/ዘመን ተቆጥሯል።
የአማራ ሕዝብ በማንኛውም መለኪ የተሻለ ሆኖ ሳለ ለዚህ ሁሉ መከራና ግፍ የተዳረው ባለመደራጀቱ፤ አንድ ባለመሆኑና ባለመመካከሩ ነው።
ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ያልተደራጀ ተፈጀ እንዳሉት ባለመደራጀታችን ጸረ አማራዎች ፈጅተውናል፤ ጨፍጭፈውናል። ተጨማሪ ፍጅቶችንም ደግሰው እየመጣንላችሁ ነው ብለው በሬንጀር እያስፈራሩ ነው።
ጣሊያንን ያሸነፍን አማሮች፤ የኦሮሞ ልዩ ኃይል የሚፎክርብን ለምንድነው የሚለው በሁላችንም አዕምሮ ውስጥ ሊመላለስ ይገባል።

በመላው አለም የምትገኙ ውድ የአማራ ልጆች እናንተ ለህዝባችሁ ስትሉ በብርድም በጸሀይም የምትችሉትን ሁሉ አድርጋችኋል ፤ እያደረጋችሁም ነው። ትግላችን ዓለም አቀፋዊ ተቀባይነት እንዲኖረው የቤተሰባችሁን ጊዜ ቀምታችሁ ሰርታችኋል፤ የተጠየቃችሁትን ሁሉ አድርጋችኋል፤ በዚህ ድርጊታችሁ ሁሉም አማራ ይኮራባችኋል። እኛ እስር ቤት ያለነው ሰዎች ሁሌም እንኮራባችኋለን።
ትግሉ የሚጠይቀውን ሁሉ እያደረጋችሁ ነውና ለዚህ ያለኝን ታላቅ አክብሮት ስገልጽላችሁ ኩራት ይሰማኛል።
በመጨረሻም ውድ ወንድም እህቶቼ የቱንም ያህል ብንሰራ አንድ ላይ ካልቋጠርነው በጎ አይደለም። ስትተባበሩና  በህብረት ስትቆሙ በባሌም፤ በጉለሌም፤ በሞያሌም ፤ በሱማሌም ያለው አማራ ቀና ብሎ ይሄዳል። እናንተ ውድ ወንድም እህቶቻችን አንድ ከሆናችሁ የማሸነፍና የመደራደር አቅማችን  (Wining and bargaining capacity ) በእጅጉ ይጨምራል።
በሃሳብ ብንለያይም የአማራ አንገቱ አንድ ነውና በአንድነት እንቁም።
ደጃዝማች ጸሀዩ እንቁስላሴና ደራሲና ዲፕሎማት ሀዲስ አለማየሁ እንዳሉት እንተባበር በጋራ እንቁም። በመካከላቸው ምስራቅ ፣ በአሜሪካ ፣ በአውሮፓ ፣ በአፍሪካና በካረቢያን ብሎም በሩቅ ምስራቅ ያሉ ሁሉም የአማራ ልጆች በህብረት ቢቆሙ ይህ አገዛዝ ሁለት ቀን የሚያድር ይመስላችኋል ? በፍጹም ።
እናም በርቱልኝ፤ አንድ ሁኑ ተዋደዱ፤ ተመካከሩ።

ድል ለአማራ ህዝብ
እርግጠኛ ነኝ ከነጻነት በኋላ እንገናኛለን ።
እወዳችኋለሁ
11.7K viewsአባ ስበር, 02:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-23 22:03:49 የሸዋው የፋኖ ተጋድሎና ድል

የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝና ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ሰራዊት በጥምረት ባደረጉት ውጊያ የአገዛዙ ጦር ሲበታትኑት ዋሉ የአማራ ፋኖ ሁለቱ የሸዋ ዕዞች በጥምረት ባደረጉት የማጥቃት እርምጃ የብልፅግናው ስልጣን ጠባቂ ኃይል በሸዋ መርሐቤቴ ከፍተኛ ሽንፈት እንደገጠመው የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ አስታውቋል።
የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ሰራዊት ዛሬ ቅዳሜ ሰኔ 15/2016ዓ/ም ከጠዋት ጀምሮ በፈፀመው ጀብዱ የአገዛዙን ሰራዊት ደባቅ መቷል።
ራሱን መከላከያ በማለት የሚጠራው የአገዛዙ ወንበር ጠባቂ  ከጎኑ ባንዳ አድማ ብተናና ሚሊሻ በማሰለፍ  መነሻውን መርሐቤቴ ዓለም ከተማ አድርጎ መድረሻውን ልዩ ቦታው  ኮለሽ በተባለ ቦታ ቢያደርግም ያሰበው ቦታ ሳይደርስ በፋኖ ተመቷል።
የዐቢይ ጦር በአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ናደው ክፍለ ጦር በተወሰደበት የደፈጣ ጥቃት በርካታ ኃይሉ  ሲደመሰሱ ከፊሉ ቁስለኛ እና እድል የቀናው ተበታትኖ ትጥቁን ለአካባቢው አርሶ አደር በማስረከብ በመፈርጠጥ ላይ መሆኑ ታውቋል።
በዚህ ምት የተበሳጨው የወራሪው ስርዓት ስብስብ ከመቃጠል እና ከምርኮ የተረፈውን ሞርታርና ዙ 23 ከርቀት  ወደ ንፁሀን አርሶ አደሮች መኖሪያ ቤት ላይ በማስወንጨፍ  ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ንፁሃን አማራዎችን ለሞትና ለአካል ጉዳት መዳረጉም ተሰምቷል።
የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ምክትል ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ንጋቱ ይታፈሩ እየወሰዱት ስላለው የማጥቃት እርምጃ ለሮሃ በስልክ ማብራሪያ ሰጥቷል።
የፋኖ አመራሩ የወገን ኃይል በከፍተኛ ሞራል እና ወኔ ሙሉ ለሙሉ  ጠላትን ለመደምሰስ እና ድሉን ለማብሰር ወደ ፊት በመገስገስ ላይ እንደሚገኝ ነግሮናል።
ፋኖ ንጋቱ የዛሬውን ጦርነት ልዩ ከሚያደርገው ነገር አንዱ የፋኖ ኃይል አንድነት የታየበትና የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ እና የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ሰራዊት በጋራ በመሆን ድል መቀዳጀታቸው መሆኑን ጠቅሷል።
የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት የአፄ ዳዊት ክፍለ ጦር አስማረ ዳኜ ብርጌድ ሰራዊት በአገዛዙ ጦር ላይ ጠንካራ እርምጃ መውሰዱንም የሸዋ ዕዝ ምክትል ህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አስረድቷል።
10.8K viewsአባ ስበር, 19:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-23 20:29:33 #የተቀናጀ_ጥቃት…

በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ከመርሐቤቴ ዓለም ከተማ ወደ ኮለሽ ሲጎዝ የነበረው የኦነግ ብልፅግና መከላከያ እስከ ባንዳ አድማ ብተና እና ሚሊሻ ድባቅ ተመቷል::

በትላንትናው ዕለት የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ናደው ክፍለጦርና  የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አጼ ዳዊት ክፍለጦር አስማረ ዳኜ ብርጌድ በመናበብ ጠላት ላይ ባደረጉት ድንገተኛ ጥቃት የኦሮሙማው አራዊት ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ ተደርጏል:: በዙ23ና ሞርተር ጨምሮ በንፁሃን አማራዎች ቤቶች ላይ በከባድ መሳሪያ ሲተኩስ የነበረው የኦሮሙማው አራዊት ከፍተኛ ቁጥር ያለው የፋኖ ጥይት ሲሳይ ሆኖ ከሞት የተረፈው የተከመረውን አስክሬን ሳያነሳ ወደ አለም ከተማ ፈርጥጧል::

16/10/16 ዓ.ም
10.8K viewsEd1, 17:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ